INDUSTRIAL ZONE : OROMIA REGIONAL STATE

1 ሺህ ሄክታር መሬት ከሊዝ ክፍያ ነፃ እንዲሰጥ ተጠየቀ
የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በካሬ ሜትር 7 ብር አቅርቧል

በጋዜጣው ሪፖርተር

አክ ጉን ኢንሳት የተባለው የቱርክ ኩባንያ በለገጣፎ እገነባለሁ ላለው የቱርክ ኢንዱስትሪ ዞን የሚሰጠውን አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ከሊዝ ክፍያ ነፃ እንዲደረግለት ጠየቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በካሬ ሜትር 7 ብር እንዲከፍሉ ጠይቋል፡፡

ኩባንያው ጥያቄውን ያቀረበው ለፌዴራልና ለክልሉ መንግሥታት በላከው የኮንትራት ስምምነት ውል ረቂቅ ሰነድ ላይ ሲሆን ረቂቁ ከፌዴራል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በተውጣጡ ባለሙያዎች ተገምግሞ አስተያየት እንደተሰጠበት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የይግባኝ ጉዳዮች ሥራ ፈፃሚ የሆኑት አቶ አብዱልሀኪም ሙክታር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ሙክታር ገለፃ አክ ጉን ኢንሳት የተባለው ኩባንያ ለፌዴራል መንግሥትና ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያቀረባቸው ጥያቄዎች የተለያዩ ናቸው፡፡

ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የመሬት ኪራይ ነፃ እንዲደረግለትና ለፕሮጀክቱ የተጠየቀው መሬት ከሊዝ ክፍያ ነፃ እንዲሰጠው የሚጠይቀው የውል ኮንትራት ረቂቅ ለኦሮሚያ ክልል የቀረበ ሲሆን ለፌዴራል መንግሥት የቀረበው ጥያቄ ደግሞ የታክስ አከፋፈል፣ የጉምሩክ ጉዳዮች፣ የደህንነት ዋስትናና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከሚያስፈልገው ወጪ 30 በመቶ ያክሉ በመንግሥት እንዲሸፈን የሚጠይቅ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረት ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከሚወጣው አጠቃላይ ወጪ 205,340,000 ዶላር ውስጥ መንግሥት 61 ሚሊዮን 602 ሺህ ዶላር የሚሆነውን ወጪ እንዲሸፍን በረቂቅ ሰነዱ ተጠቁሟል፡፡

ከንግድና ኢንዱስትሪ አንድ የህግ ባለሙያና ኤክስፐርት፣ ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሁለት የሕግ ባለሙያዎች ሰነዱን መርምረው የፌዴራልና የክልሉን መንግሥት ሕግ መሠረት ባደረገ መልኩ ማስተካከያ ተደርጐበት ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አባዱላ ገመዳና ለፌዴራል የንግድና ኢንዲስትሪ ሚኒስትር ግርማ ብሩ መቅረቡን አቶ አብዱልሀኪም አስታውቀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በኩል ከኩባንያው ለቀረበው የሊዝ ነፃ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ በካሬ ሜትር 7 ብር ወይም 0.54 ሣንቲም በዶላር እንዲከፍሉ በረቂቅ የኮንትራት ውሉ ላይ መገለፁን የጠቆሙት አቶ አብዱልሀኪም "እየተደረገ ያለው የድርድር ሂደት በመሆኑ ማስተካከያ የተደረገበት ረቂቅ ሰነድ ወደ ቱርክ ተልኮ ምላሽ ከተሰጠበት በኋላ ወደ ውል ስምምነቱ እናመራለን" በማለት ተናግረዋል፡፡

የቱርክ ኢንዱስትሪያል ዞን ፕሮጀክት 890 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን ባለፈው ዓመት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍንን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልሉ ባለሥልጣናት እንዲሁም ፕሬዚዳንቱ አባዱላ በተገኙበት ከኩባንያው ባለሀብቶች ጋር በሂልተን ሆቴል ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡-

I am glad these businesses are coming, but the deals seem to be just giving shit away for free. We need good negotiators in these meetings, because it sounds like we are giving too much in these deals. Oh well, here we come globalization.

http://www.ethiopianreporter.com/ind…-10&Itemid=617